በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል;ግምገማና ሪፖርት አቀራረብን በተመለከተ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
Posted by admin on Friday, 17 January 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (BHU)
የአቅም ግንባታ ስልጠናዉ የተዘጋጀዉ በትምህርት ሚኒስቴርና በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ የጋራ ትብብር ሲሆን ሥልጠናው የተሠጠው ለኮሌጅ ዲኖች; ለዳይሬክተሮች; ለሥራ አስፈጻሚዎች; ለትምህርት ክፍሎችና ለአስተባባርሪዎች ነው።
የሥልጠናው ዋና ዓላማ በዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል; ግምገማና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ የሚስተዋለውን ክፍተትና የአቅም ውስንነት ችግሮችን በመቅረፍ የታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተገልጿዋል።
በሥልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ሲሆኑ የስልጠናዉን አስፈላጊነት በሚመለከት መሠረታዊና ቁልፍ መልዕክቶችን ለሠልጣኝ ባለሙያዎቹ አስተላልፏል፡፡