በቡሌ ሆራ ማስተማሪያ ሆስፒታል አንድ ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከአንድ ታካሚ አንገት ላይ ተወግዷል።

ህዳር 06/2016 ዓ.ም
ታካሚዋ ከአምስት አመት በላይ አንገቷ ላይ እጢ የነበረባት  ሲሆን በሆስፒታሉ ውስጥ የተለያዩ ምርመራ እና ህክምና ከተደረገላት በኋላ እጢው ያለምንም ችግር ተወግዶላታል።
በቡሌ ሆራ መማሪያ ሆስፒታል ውስጥ በተለያዩ ህክምና ዘርፍ ላይ ስፔሻላይዝ ያደረጉ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ስላሉ ህብረተሰቡ ይህንን  ተረድቶ  እንዲጠቀምበት የሆስፒታሉ ማኔጅመንት እስታውቋል::