በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የሠራተኞች ምደባ መዋቅር መሠረት ወደ ትግበራ ለመግባት የአስተዳደር ሠራተኞች ምደባ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄደ፡፡ 

ህዳር 06/2016 ዓ.ም
በሲቭል ሰርቭስ ሚኒስቴር በኩል ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የሠራተኞች ምደባ መዋቅር መመሪያ መላኩ ይታወሳል፡፡
ስለሆነም በመጣዉ መወቅር መሠረት ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ የሠራተኞችን ምደባ ለማካሄድ እንድያስችል በዛሬው ዕለት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማና የሠራተኞችና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ገመዳ ኦዶ  በተገኙበት በመዋቅሩ መሠረት ምደባውን የሚያካሂዱ የሠራተኞች ተወካዮች ተመርጧል፡፡ ምርጫው የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ኦዳ አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን ሦስት ተወካዮች ማለትም 1ኛ አቶ ጋላቶም ብሩ ፣ 2ኛወ/ሮ ሲንቦ አየለ  3ኛ አቶ ዋቆ ኩሬ በመሆን ፍታሃዊና አሣታፊ በሆነ መልኩ በድምጽ ብልጫ ተመርጠዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ በመዋቅሩ መሠረት ምደባውን የመካሄዱ ጉዳይ ግልጽ በሆነና ለእያንዳንዱ ሠራተኛ በመዋቅሩ ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ጭምር የሚሠራ መሆኑን በመግለጽ ሥራው በበላይ አመራሮች በኩልም አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡