የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ፈተና የሚወስዱትን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል።

መስከረም 24/2014 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ፈተና የሚወስዱትን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመግቢያ ፈተና በት/ቤቶች ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ዘንድሮ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት የ2014 የ12ኛ ክፍል በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ፈተና ይወስዳሉ።

በቡሌ ሆራ  ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው የአሥር ዓመት የሥራ  ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

25/12/2014
የቡሌ ሆራ  ዩኒቨርሲቲ  ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ ከዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላት ጋር በዩኒቨርሲቲው የአሥር ዓመት የሥራ  ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡ 
በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶችን  ጨምሮ የካውንስል አባላቶች ተገኝተዋል፡፡ ከመማር ማስተማር፣ ከምርምር ፣ ከማህበረሰብ አገልግሎት ፣ ከኢንዱስትሪ ትሥሥር  እና ከአጠቃላይ ተቋማዊ የሥራ ትግበራ አንጻር ከ2010 እሰከ 2014 ዓ.ም ድረስ የዩኒቨርሲቲው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በውይይቱ የቀረበ ሲሆን ከ2015 እሰከ 2024ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን የልህቀት ደረጃ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀው የተቋሙ ዕቅድም ለካውንስል አበላቱ ቀርቧል፡፡ 

የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ቦርድ በሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አደረገ

ነሐሴ 22/2014 ዓ.ም
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ቦርድ በሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አደረገ። በውይይቱ የሆስፒታሉ ቦርድ አደረጃጀት፣የሆስፒታሉ ቦርድ አመራር ሀላፊነት፣ ክትትል እና ምዘና እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ሂደት በስፋት ተብራርቷል ።
የሆስፒታሉን አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ከማሻሻል አንፃር የሆስፒታሉ ቦርድ ሊኖረው ስለሚገባው ሀላፊነትም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳቢና የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ረ/ፕ ገመዳ ኦዶ የሆስፒታሉ የቦርድ አመራር ፤ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተቀናጀ እና በተናበበ መልኩ በመስራት የሆስፒታሉን አገልግሎት አሰጣጥ ወደሚፈለገው ደረጃ ማድረስ የጋራ ሀላፊነት መሆኑን በመጠቆም የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ቦርድ አመራር ተገቢውን የድጋፍ እና ክትትል ስራ ማከናወን እንዳለበት ገልፀዋል።

Pages