የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ፈተና የሚወስዱትን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል።

መስከረም 24/2014 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ፈተና የሚወስዱትን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመግቢያ ፈተና በት/ቤቶች ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ዘንድሮ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት የ2014 የ12ኛ ክፍል በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ፈተና ይወስዳሉ።
የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲስጥ መደረጉን ተከትሎ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች ዩኒቨርሲቲው ሙሉ ዝግጅቱን ስለማጠናቀቁ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሮባ ዳንቢ ገልጽዋል:: የምግብ፣በቂ እና ንፁህ የመኝታ ክፍሎች፣እንድሁም የመፈተኛ ክፍሎች እና ወንበሮች የት/ት ሚኒስቴር መመሪያን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን እና ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድርሰ አስተማማኝ በሆነ መልኩ ከም/ጉጅ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባባር የሠላም እና ደህንነት የዝግጅት ስራ መከናውኑንም ዶ/ር ሮባ ዳንቢ ገልፀዋል::
ከዚህ ቀደም የፈተና ስርቆት እየጨመረ በመምጣቱ አንዳንድ ተማሪዎች እራሳቸው ሰርተው ያላገኙትን ውጤት ይዘው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባታቸው ለውድቀት ዳርጓቸዋል። ይህ ደግሞ በሀገሪቱ የትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስላለው መንግስትም ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የዘንድሮውን ሀገር አቀፍ የመልቀቅያ ፈተና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መስጠት እንዳለበት መወሰኑም ይታወቃል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን የሚወስዱ ከ23,165 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ስሆን፤በመጀመሪያው ዙር ላይ 15,528 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከመስከረም 26-28/2015ዓ.ም የምቀበል ስሆን፤ከእነዚህ ውስጥ 7,497 ሴቶች መሆናቸው ታውቆዋል። ስለዚህ በዩንቨርሲቲው ለምቆዩ ተማሪዎች የማረፊያ፣ የምግብ፣ የመፈተኛ ክፍል እንድሁም የተማሪዎችን ደህንነትና ጤና ከማረጋገጥ አኳያ ሁሉም ነገር መጠናቀቁን ገልጾዋል።
በተጨማርም የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር መ/ር ሀሮ ዱሎማ እንደተናገሩት እንደ ተማሪ አገልግሎት በሦስት ዋና ዋና ነገሮች ማለትም የተማሪዎች ምግብ፣ የማረፊያና የተማሪዎች ክሊኒክ በጥሩ ሁኔታ አዘጋጅተናል ብለዋል። በሌላ በኩል ለተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ለፈተና የሚመጡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ላይ ግንዛቤ ተሰጥቷቸዋል።
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ