የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡
Posted by admin on Saturday, 10 June 2023ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ኢንተርፕራይዝ የተዘጋጀውን በመግዛት የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገልፀዋል፡፡የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም የተገዛውን የስንዴ ምርጥ ዘር ለምዕራብ ጉጂ ዞን ም/አስተዳዳሪ ርክክብ ባደረጉት ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዉ የልህቀት ማዕከል አደርጎ ከሚሰራባቸዉ ሥራዎች አንዱ የግብርና ልማትን ማስፋፋት መሆኑን በመጥቀስ ይህ እየተከፋፈለ ያለዉ የስንዴ ምርጥ ዘር በአምስቱ ወረዳ ዉስጥ ላሉና በይበልጥ በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸዉ የህበረተሰብ ክፍል መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዉ ተመሳሳይ ሥራዎችን በማህብረሰብ አገልግሎት በኩል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል፡፡