የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ  ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡

ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ  ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ኢንተርፕራይዝ የተዘጋጀውን  በመግዛት  የስንዴ ምርጥ ዘር  ማከፋፈሉን ገልፀዋል፡፡የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም የተገዛውን  የስንዴ ምርጥ ዘር ለምዕራብ ጉጂ ዞን ም/አስተዳዳሪ ርክክብ ባደረጉት ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዉ የልህቀት ማዕከል አደርጎ ከሚሰራባቸዉ ሥራዎች አንዱ የግብርና ልማትን ማስፋፋት መሆኑን በመጥቀስ ይህ እየተከፋፈለ ያለዉ የስንዴ ምርጥ ዘር በአምስቱ ወረዳ ዉስጥ ላሉና በይበልጥ  በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸዉ የህበረተሰብ ክፍል  መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዉ ተመሳሳይ ሥራዎችን በማህብረሰብ አገልግሎት በኩል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል፡፡   
በሌላ በኩል በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታደሰ ጅሎ እንደገለፁት ቀደም ሲል ለአምስቱ ወረዳዎች ዩኒቨርሲቲዉ ነፃ የህግና የጤና አገልግሎት እየሰጠ የቆየ መሆኑን አስረድትዋል::  ከስንዴው ምርጥ ዘር ጋርም በተያያዘ ዩኒቨርሲቲዉ በአጠቃላይ 389 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር  በሁለት ሚሊዮን ብር መገዛቱን አሳውቆ ከዚህም ላይ 355 ኩንታል  ለአምስት ወረዳ አርሶ አደሮች የተሰጠ ሲሆን ቀሪው 34 ኩንታል ለዩኒቨርሲቲው ግብርና ማዕከል ገቢ መደረጉን ገልፀዋል፡፡