በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ህክምና ዘመቻ ሥራ ከእቅድ በላይ በመፈፀም ተጠናቀቀ።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከሐምሌ 7-11/2017 ዓ.ም ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከክፍያ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ህክምና ዘመቻ ሥራ ለ500 ግለሰቦች አግልግሎቱን ለመስጠት ታቅዶ ለ523 ሰዎች ነፃ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ህክምናውን ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ ለመጡ ነገር ግን በተደረገው ምርምራ የአይን ሞራ ግርዶሽ ጋር ያልተገናኘ ለ1200 ሰዎች ጭምር ነፃ ምርምራና አስፈላጊውን መድሃኒት በመስጠት በስኬት ስለ መጠናቀቁ ተገልፆዋል።



















































