በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ጆርናሎችን ለማቋቋም በቀረበዉ ጽሑፍ ላይ የዉጭ ምሁራን በተገኙበት ግምገማ ተካሄደ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 08፣ 2018 (ቡሆዩ)

በዩኒቨርሲቲዉ ቀደም ሲል ከነበሩት ጆርናሎች በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ጆርናሎችን ለማቋቋም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማን ጨምሮ የአካዳሚክ፤ ምርምር፤ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ፤የዩኒቨርሲቲዉ ምሁራንና በዘርፉ ልምድ ያካበቱ የሌሎች ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጭምር በተገኙበት የጆርናሎቹ ረቂቅ ጽሑፍ ቀርቦ ግምገማ ተካሂዶባቸዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዉ ምርምር፤ሥነ-ምግባርና ስርጸት ዳይሬክቶሬት በኩል ለመቋቋም ተጠንተዉ የቀረቡ ጆርናሎች "HORAA Journal of Social Science and Humanities" እና "Ethiopian Journal of Interdisciplinary Natural Science " የሚሉ ስያሜዎችን የያዙ ጆርናሎች ጽሑፍ እና የጆርናሎቹ ሎጎ የቀረቡ ሲሆኑ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ የመጡ አራት የጆርናሎች ኤዲቶሪያል ቦርድ አባል የሆኑ ምሁራን በቀረበዉ ረቂቅ ጽሑፍ ላይ ሙያዊ ትንታኔና ግምገማ አቅርቧል፡፡

በዩኒቨርሲቲዉ በኩል ጽሑፉን ያቀረቡት መ/ር ገብሬ ጋርማሜ "HORAA Journal of Social Science and Humanities" እና ዶ/ር አበበ ገመቹ ከግብርና ኮሌጅ "Ethiopian Journal of Interdisciplinary Natural Science" ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ የተሰጡ አስተያየቶች ተጨምረዉ የሚመለከታቸዉ የዩኒቨርሲቲዉ ምሁራን በተገኙበት እንደምፀድቅ ተገልጾዋል፡፡

በዕለቱም የመዚጊያ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚክ፤ ምርምር፤ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመምጣት ልምዳቸዉን ላከፈሉ ምሁራን ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም በጋራ ለመሥራት ዩኒቨርሲቲዉ ቁርጠኛ መሆኑን አስረድቷል፡፡