በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸዉን እየተከታተሉ ለሚገኙ የ2ኛ ዓመትና ከዚያን በላይ ለሆኑ መደበኛ ተማሪዎች የ‹‹e-SHE ( Student Success Suit ) የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ቡሆዩ)

የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመሩ በፊት የe-SHE አስፈላጊነትና አጠቃቀምን በሚመለከት በኢ-ሌርንግ ማናጅመንት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለመደበኛ ተማሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

ሥልጠናዉን የሰጡት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢ-ሌርንግ ማናጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ንጉስ ቢተዉ ሲሆኑ ይህ በመማር ማስተማሩ ሂደት ወሳኝ ድርሻ ያለዉ በመሆኑና በቀጣይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ የበይነ መረብ የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ትኩረት ሰጥተዉ እንዲከታተሉ በአንክሮ አሳስቧል፡፡

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ጆርናሎችን ለማቋቋም በቀረበዉ ጽሑፍ ላይ የዉጭ ምሁራን በተገኙበት ግምገማ ተካሄደ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 08፣ 2018 (ቡሆዩ)

በዩኒቨርሲቲዉ ቀደም ሲል ከነበሩት ጆርናሎች በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ጆርናሎችን ለማቋቋም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማን ጨምሮ የአካዳሚክ፤ ምርምር፤ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ፤የዩኒቨርሲቲዉ ምሁራንና በዘርፉ ልምድ ያካበቱ የሌሎች ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጭምር በተገኙበት የጆርናሎቹ ረቂቅ ጽሑፍ ቀርቦ ግምገማ ተካሂዶባቸዋል፡፡

Pages