​​​​​​​በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነርንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነርንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ለሚማሩ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።    ሐምሌ 23፣ 2014ዓ.ም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ምክትል ዲን ኢንጂነር ዳስታ ጋማዳ ተማሪዎቹ ወደ ኮሌጁ ለመግባት ፍላጎታቸው እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በአገር አቀፍ ደረጃ የፋብሪካዎች መስፋፋት እየጨመረ በመምጣቱ ሀገሪቱ ተጨማሪ ኢንጂነሮች ያስፈልጋታል ሲሉም ተናግረዋል።በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ አስራ ሁለት (12) ትምህርት ክፍሎች እንዳሉት እና አላማዎቻቸውንም  ያብራሩት በኮሌጁ የአካዳሚክ ጥራት አስተባባሪ መ/ር ይድነቃቸው ዋዳአ እና የፕሪ እንጂነርንግ አስተባባሪ መ/ር ደራጄ አርጃሞ ናቸው።የስልጠናው አላማ ተማሪዎች ከአካዳሚክ ህይወት በኋላ የጥገኝነት አስተሳሰብ እንዳያዳብሩ እና ወደ ንግዱ አለም ገብተው በእውቀታቸው እንዲለወጡ ያላቸውን ግንዛቤ ማጠናከር ነው።በስልጠናው ላይ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ስር

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የ2014 ዓ.ም አፈፃፀም ረፖርት፣

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የ2014 ዓ.ም አፈፃፀም ረፖርት፣
የ2015 ዓ.ም የጸደቀ በጀት፣ የ2015 ዓ.ም የግዥ ፍላጎት እንድሁም አዲስ የሰራተኛ መዋቅር ላይ ውይይት አደረጉ::
ውይይቱ 4 መሰረታዊ አጀንዳዎችን የያዘ ሲሆን፡-
1. የ2014 ዓ.ም የስራ አፍፃፀመ ረፖርት
2. የ2015 ዓ.ም የግዥ ፍላጎት
3. የ2015 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲው በጸደቀ በጀት እና
4. አዲስ የሰራተኞች መዋቀር ዙሪያ በውይይት ተካይድዋል::

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለአትሌቶችን ምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለአትሌቶችን ምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።
ሐምሌ 21/2014 (ቡሆዩ)የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለጀግኖች አትሌቶች በ18ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ከዕለም ሁለተኛ ከአፍሪካ አንደኛ ሆነዉ ድል ላስመዘገቡት የምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ (ፒኤችዲ) ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደ ሀገር ፈተና ያጋጠመን ቢሆንም ሳንደነቃቀፍ የኢትዮጵያን አኩሪ የድል ታሪክ መጻፍ የቻልን ትውልድ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ
*****
በዉይይት መድረኩ ላይ በአገራዊ እና በተቋማዊ የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ በተባባሪ ፕሮፌሰር ጫላ ዋታ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የቀረበዉ የመነሻ ሀሳብ ጭብጦች፡ የ2015 ዓ.ም በአገራዊ የትኩረት አቅጣጫ አንኳር ጉዳዮች፤ የትምህርት ዘርፉን ቀጣይ አቅጣጫዎች ለምሳሌ፡-የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ማረጋገጥ፣ሌብነትንና ብክነትን መታገል፤ ፉትሃዊ ቅጥር፣ ምደባና አገልግሎት ማረጋገጥ፤ አካባቢያዊነትን መታገል፤ ፖለቲካና ትምህርትን መለየት-ሴኩላሪዝምን ማረጋገጥ፤ ራስ-ገዝነትን እና የቦርድ ሚና ማጠናከር ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡

Pages