የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የተቋሙን የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት የውስጥ ገቢ እቅድ ግምገማ አካሄደ።
የካቲት 26/2018 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ሪፖርቱን ያቀረቡት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ መሰለ አለማየሁ ሲሆኑ፣ ቁልፍ የውጤት አመላካቾችን አፈፃፀም በየሥራ ዘርፋቸዉ አንፃር በማደራጀት በመማር ማስተማር ፣በምርምር፣ በማህብረሰብ አገልግሎት፣ በአስተዳደር ዘርፍ እና በተቋሙ የልህቀት መስኮች የተከናወኑ ተግባራትን መሠረት በማድረግ ነዉ።
በኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶክተር ኬይረዲን ተዘራና የቦርድ አባላት፣ ከዶክተር ተመስገን ደበሎና ከእጩ ዶክተር ታሪኩ ገመዴ ጋር የትውውቅ መርሐ ግብር ካካሄዱ በኋላ፣የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና በልዩ እቅድ በተያዘዉ ከታህሳስ 14 -እስከ የካቲት 23/2018 በ70 ቀናት የተከናወኑ ተግባራት እቅድ ግምገማ በማካሄድ የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በተጨማሪም አቶ መሰለ አለማየሁ ለስራ አመራር ቦርድ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የውስጥ ገቢ ዕቅድና ተቋሙ በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙት ችግሮች፣ ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችንም በዝርዝር አቅርቧል።
በውይይቱ መጨረሻም የተለያዩ ሀሳቦች ከዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተመስገን ደበሎ እና ም/ፕሬዝዳንቶች የየራሳቸዉን ሃሳብ በማንሳት፣ ተቋሙ በምቹና መልካም መልከዓ ምድር ከመገኘቱ አንጻር በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ወደፊት ለማራመድ ሁሉም ባለድርሻ አካል መረባረብ እንደሚገባውና በቀጣይ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራሰገዝ በሚያደርገው ሂደት በውስጥ ገቢ እራሱን ችሎ በተማሪዎች እንዲሁም በተመራማሪዎች ተመራጭ እንዲሆን መትጋት አስፈላጊ እንደሆነ ዶክተር ኬይረዲን ተዘራ አቅጣጫ አስቀምጠው፣ በመጨረሽም የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የውስጥ ገቢ ዕቅድና ዩኒቨርስቲው ሲጠቀምበት የቆየዉን አርማ (ሎጎ) ማሻሻያ በማድረግና ለዉይይት በማቅረብ የጋራ መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ በማጽደቅ ውይይቱ ተጠናቋል።




















































