የዋቢ መጽሐፍት ድጋፍ ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት

የዋቢ መጽሐፍት ድጋፍ ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የህንድ አገር ተወላጅ መምህራን በአገራቸው OTF(Ontaro Teachers Federation) ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ሲሆን፤ ከ1ኛ-8ኛ እንዲሁም ከ9ኛ-10ኛ ክፍል የማጣቀሻ መጻሕፍት ድጋፍ ለትምህርት ቤቱ አስረክበዋል ። በድጋፍ የተበረከተው መጽሐፍት ብዛት ከ5-8ኛ ክፍል 480፣ ከ9-10ኛ ክፍል 280 በአጠቃላይ 760 መጽሐፍት ነዉ።
የመጽሐፍቱ ድጋፍ በዓይነት ባዮሎጂ ፣ ኬሚስትሪ ፣ ፊዚክስ ፣ ሂሳብ ፣ጅኦግራፊ እና የእንግሊዝ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ሲሆኑ ፤ ተማሪዎች እና መምህራን ለተደረገላቸው የዋቢ መጻህፍት ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመሥግነዋልም። የመጽሐፍቱን ርክክብ መርሃግብር ላይ የአካዳሚክ ጉዳይ ም/ፕረዚዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ እና የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕረዚዳንት ዶ/ር ጉሚ ቦሩ በተገኙበት ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ለአቶ በሪሶ ዳጋ አስረክበዋል ።
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን !!!
ጥር 13/2014 ዓ.ም
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ