የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢኒስቲቲዩት እጩ ምሩቃን ሲሰሩ የቆዩትን ምርምር አቀረቡ

ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢኒስቲቲዩት እጩ ምሩቃን ከኢኒስቲቲዩቱ ጋር በመተባበር በማህበረሰብ ጤና ዙሪያ ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲሰሩት የቆዩትን ምርምር አቀረቡ።
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ገመዳ ኦዶን ጨምሮ የጤና ኢኒስቲቲዩቱ መምህራንና የኢኒስቲቲዩቱ  እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ተገኝተዋል። የማህበረሰብን የጤና ችግር ለመፍታት የተደረገዉ Team Training Program(TTP)በተለያዩ አራት ወረዳዎች ሲሆን ዱግደ ዳዋ፣ቡሌ ሆራ፣ ያቤሎ እና ጓንጓ ጥናቱ የተደረገባቸው ወረዳዎች ናቸው።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢኒስቲቲዩት የማህበረሰብ መርህ አስተባባሪ መምህር ጂቱ ቤካ የ Team Training Program (TTP) ወደ ማህበረሰብ ወርዶ የማህበረሰብን የጤና ችግር በመመርመር ለማህበረሰብ ጤና ከመስራት ባሻገር በጋራ የመስራት ባህልን ለማሳደግ እና እውቀትን ለመቅሰም ጠቀሜታው የላቀ እንደሆነ ተናግረዋል። ከመደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት በተጨማሪ ተማሪዎች ወደ ማህበረሰብ በመውረድ በማሃበረሰብ ጤና ዙሪያ እንዲሰሩ ማድረግ የዉይይት ክህሎትን ለማሳደግና የጥናታዊ ጽሁፍ አጻጻፍ አቅምን ለማጎልበት እንደሚጠቅም መምህርት ጂቱ ቤካ አክለው ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲው የጤና ኢኒስቲቲዩት አካዳሚክ ዳይሬክተር መምህር ቦኮ ሎኮ በበኩላቸው የጤናው ዘርፍ በጋራ መስራትን የሚጠይቅ በመሆኑ የኢኒስቲቲዩቱ እጩ ተመራቂዎች በጋራ የመስራት ባህልን እንዲያዳብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ