በኢትዮጵያ የUNFPA & KOICA ኃላፊዎች የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎብኙ፡፡

ህዳር 01/2016 ዓ.ም 
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነቶችን በመፈራረም በጤናው ዘርፍ አመርቂ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የጋራ የሥራ ስምምነቱን በመፈፀም ከማስተማሪያ ሆስፒታሉ ጋር እየሠሩ ካሉ ድርጅቶች መካከል የUNFPA & Korea International Cooperation Agency (KOICA) ዋነኞቹ ሲሆኑ የድርጅቶቹ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ልዑካን ቡድኖችን ጨምሮ በድርጅቱ ድጋፍ በማስተማሪያ ሆስፒታሉ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በድርጅቱ ድጋፍ የተቋቋመውን ማዕከል ጉብኝት የመሩት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጤና ኢንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ ናቸው። 
በሆስፒታሉ ዉስጥም bule Hora one-Stop Center በሚል ራሱን የቻለ ማዕከል ተቋቁሞ በጤናው ዘርፍ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን አስረድተው
 በማዕከሉ እየተሰጡ ያሉ የጤና አገልግሎቶችን ገለፃ ያደረጉት ዶ/ር ሳፋይ በእናቶችና በህፃናት ላይ ለየት ያለ ትኩረት በመስጠት እየሠሩ ያሉ ድርጅቶች መሆናቸውን በመጥቀስ ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የቀዶ ጥገና ህክምናዎችም በልዩ ድጋፍ የሚሰጡ ስለ መሆናቸውም ተናግረዋል፡፡
በሌላ መልኩ በጉብኝቱ ወቅት መግለጫ የሰጡት የድርጅቶቹ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኘው ድጋፍ የማስተማሪያ ሆስፒታሉ እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቀው በስምምነቱ መሠረት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራ ከተጠናቀቀ ቦኃላ ለቀጣይ ሆስፒታሉ በሚያቀርበው