በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ሥራ ጋር የተያያዘ ስልጠና

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ሥራ ጋር የተያያዘ ስልጠና
*******
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በፕሮፖዛል አዘገጃጀት፣ በፕሮጀክት አቀራረፅ እና ሌሎች ከምርምር ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ሥልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ኮሌጆችና እንሰቲቲዩቶች ለተውጣጡ መምህራኖች ሲሆን፤ ሥልጠናው ከጥር 14-17/2014 ዓ.ም ላለፉት ሦሥት ቀናት በተከታታይ ሲሰጥ ቆይቶ ነጌ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ሥልጠናው የተዘጋጀው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕ/ጽ/ቤት ሲሆን፤ በዘርፉ ልምድና ዕውቀትን ያካበቱ ምሁራን ሥልጠናውን ለመምህራን ሲሰጡ ቆይተዋል።
በስልጠናው መግቢያ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ጉሚ ቦሩ (የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕረዚዳንት ) መምህራ ከመማር ማስተማር ጐን ለጐን የምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በመጠቆም “የማህበረስብን እና የሀገርን ጥቅም የሚያረጋግጡና ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮችን ለመስራት ዩኒቨርሲቲው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ያደርጋል“ ብለዋል።
ስልጠና የተሰጠው ለተከታታይ አራት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፤ ነጌ ጥር 17/2014 ዓ.ም ከሰዓት የሚጠናቀቅ ሆኖ፤የመምህራንን የምርምር አቅም እና ተነሳሽነትን ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።“
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን !!!
ጥር 16/2014 ዓ.ም
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ