Bule Hora University Establishes Connections with University College Dublin (UCD)
Posted by admin on Thursday, 31 July 2025በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ህክምና ዘመቻ ሥራ ከእቅድ በላይ በመፈፀም ተጠናቀቀ።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከሐምሌ 7-11/2017 ዓ.ም ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከክፍያ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ህክምና ዘመቻ ሥራ ለ500 ግለሰቦች አግልግሎቱን ለመስጠት ታቅዶ ለ523 ሰዎች ነፃ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ህክምናውን ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ ለመጡ ነገር ግን በተደረገው ምርምራ የአይን ሞራ ግርዶሽ ጋር ያልተገናኘ ለ1200 ሰዎች ጭምር ነፃ ምርምራና አስፈላጊውን መድሃኒት በመስጠት በስኬት ስለ መጠናቀቁ ተገልፆዋል።
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ``Cure Blindness``ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በዘመቻ መልክ እየተሰጠ ይገኛል።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም
በሀገራችን በአይን ህክምና ዙሪያ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከሚሠሩት ግብረሰናይ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ``Cure blindness project``ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፍጠር ለበርካታ ዞሮች ከክፍያ ነፃ የሆነ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ከመስጠቱም በላይ በርካታ የህክምና መሣሪያዎችን ጭምር ለግሷል።
በመሆኑም በተመሳሳይ መልኩ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ከሐምሌ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የአይን ህክምና አገልግሎት በዘመቻ መልክ በማስተማሪያ ሆስፒታሉ እየተሰጠ ይገኛል።


















































