የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በመምጣት ከገደና ባህል ጥናት ኢንስቲትዩት ምሁራን ጋር የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ።
Posted by admin on Thursday, 9 October 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ቡሆዩ)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሀገር በቀል ዕዉቀትን እንድ አንድ የልህቀት ማዕከል በማድረግ የገዳና ባህል ጥናት ኢንስቲትዩት በመክፈትና ዘመናዊ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ ተማሪዎችን እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ድረስ እያስተማረ ከመሆኑም ባሻገር የገር በቀል ዕዉቀት ለሕዝቦች ሠላምና አንድነት ያለዉን ፋይዳ የጎላ መሆኑን በመገንዘብ በቀጣይም በዘርፉ የተሻለና የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት ዉጭ ሀገር ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ጭምር ትስስር በመፍጠር እየሠራ ይገኛል፡፡


















































