የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጡ።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፣ ግንቦት 24፣2017 ዓ.ም (ቡሆዩ)
በሥልጠናው ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና በየደረጃው ያሉ የካውንስል አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ በሥልጠናው ቦታ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ሥልጠናው በመንግስት ደረጃ ከተሰጠን ተልዕኮና ዓላማ አንፃር በምን ደረጃ ላይ እንዳለን ራሳችንን የምንፈትሽበትና የታዩብን ውስንነቶች ካሉም በቀጣይ አሻሽለን በተሟላ ሁኔታ መፈፀም እንዲንችል አቅጣጫ የሚያሳየን ሥልጠና ነው በማለት የገለፁ ሲሆን ይህንኑ በሚመለከት ሥልጠናውን ለመስጠት በዩኒቨርሲቲው የተገኙትን የትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎችን አመስግኗል።
























































