ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከፋነ - አጋ ፋዉንዴሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡
Posted by admin on Tuesday, 2 December 2025ህዳር 20/2018 ዓ.ም፡ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ይህ ምሥረታ ወይም ፋዉንዴሽኑ ህዳር 23/2016 ዓ/ም በይፋ ስራ የጀመረ ሲሆን ፤ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ቀደም ሲል 72ኛ የጉጂ አባ ጋዳ በነበሩና የክብር ዶኮቶሬት ተሸላሚ በዩባ አጋ ጤንጤኖ ተጀምሮ የነበረዉን ሪዕይ በማስቀጠል፣ ነባሩን የገዳ ስርዓት ባህላዊ እሴቶቹን ሳይለቅ እንዲጠናከር መስራት፤ የባህል ማዕከላትን ማደራጀት የመሳሰሉ ተግባራትን ማከናወን ሲሆን የታለመለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ደግሞ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የገዳ እና ባህል ጥናት እንስቲትዩት ጋር በአጋርነትና በትብብር በገዳ ስርዓት ዙሪያ አብሮ ለመስራት ይህ የመግባቢያ ሠነድ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተፈርሟል።
























































