በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ YOLK ከተባለው ግብረሰነይ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን ሀምበላ ዋመና ወረዳ በጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  በፀሐይ ሃይል የሚሠራ የሶላር ኃይል ማመንጫ አገልግሎት አስጀመረ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም (BHU)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት YOLK ከተባለ ከደቡብ ኮሪያ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን በሀምበላ ዋመና ወረዳ የኤሌክትርክ ኃይል ካልተዳረሰባቸው ት/ቤቶች አንዱ በሆነዉ ጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ሶላር ዲሽ በመግጠም ትምህርት ቤቱንና ማህብረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት የግብረሰናይ ሥራን ለመሥራት ‹‹SOLAR COW››የሚል መጠሪያ ካለው ሌላ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራርሞ ወደ ስራ እንደገባ ታውቋል።
የሶላር ኃይል ማመንጫው ሊገሳ ዋናው ዓላማ የተማሪዎችን መጠነ ብክነት ለመቀነስ፣የአከባቢው ማህበረሰቡና ቤተሰቦቻቸው በማታ የመብራት ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ሆኖ በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትንም ለመደገፍና ማሻሻል ላይ ያተኮረ ነዉ።

በዩኒቨርሲቲዉ የአካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት እና በኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ዲን የተመራውና እንድሁም በኮልጁ ስር ከሚገኙ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ጋር በመሆን ጉብኝት ተካሄደ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም (BHU)
በጉብኝቱም ወቅት የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ እና የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ዲን መ/ር ቦሩ በዴያ እንዲሁም የኮሌጁ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች መምህራን በተገኙበት የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተጎብኝተዋል።
የጉብኝቱም አላማ በኮሌጁ የሚገኙ የትምህርት ክፍሎች አሁናዊ ሁኔታዎችን መፈተሽን ዓላማ ያደረገ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው ጠንካራውን በምን መልኩ ማሰቀጠል እንዳለባቸውና እንድሁም እንደ ክፍተት የታዩትን ደካማ ጎኖች ደግሞ እንዴት ማሻሻል አንደሚቻል አቅጣጫ ያስቀመጡበት ሁኔታ የተፈጠረ ሲሆን፣በተጨማሪም በዘለቄታነት የኮሌጁን ችግሮች መፍታትና የትምህርት ጥራት ላይ በማተኮር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ በማፍራት ዓላማው እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጦ ጉብኝቱን አጠናቋል ።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ጾታ ጥቃት፤የፀረ-ኤድስ እና የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከበረ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም (BHU)
በዚህ አመት የፀረ-ፆታ ጥቃት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ ‹‹የሴቷ ጥቅት የእኔም ነዉ ዝም አልልም! ›› በሚል መሪ ቃል፤ በሌላ በኩል የፀረ-ኤድስ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ36ኛ ጊዜ ‹‹ሰብዓዊ መብት ያከበረ ኤች አይ ቭ አገልግሎት ለሁሉም!›› እንዱሁም የአካል ጉዳተኞች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ32ኛ ጊዜ ‹‹የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታችና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ!››በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲዉ የሥራ ኃላፊዎች ፤ሰራተኞችና ተማሪዎች በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ መጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 08/2017
ሥልጠናዉ የተዘጋጀው በዩኒቨርሲቲዉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ አስተባባርነት ሲሆን ሥልጠናው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በዩኒቨርሲቲዉ ካሉት የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች በተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሰጥቷል፡፡
በሥልጠናዉ ላይ ተገኝተዉ ተገቢውን መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲዉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ተስፋነሽ ኢዴኤ ሲሆኑ የሥልጠናዉ ዓለማ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ እየገቡ ያሉ ተማሪዎች በዕዉቀትና በክህሎት ላይ የተመሠረቱ ዉሳኔዎችን የመወሰን ብቃት በማዳበር በህይወታቸዉ ዉስጥ የሚገጥማቸዉን ፈተናዎች ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር ለዉጤት እንዲበቁ ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና ስለመሆኑ አስረድቷል፡፡

Pages