Open PhD Dissertation Defense

May 25, 2025 ; Bule Hora University (BHU)
Bule Hora University's College of Natural and Computational Science, Department of Applied Mathematics, genuinely hosted its third PhD dissertation defense.
The Dean of the College, Dr. Kinfe W/Giorgis, remarked that this day marked a truly historical occasion for both the College and, in particular, the Mathematics Department.

ተመራቂዎች የቀሰሙትን እውቀት የሕብረተሰቡን ችግሮች በሚፈቱ የምርምር ስራዎች ላይ ሊያውሉት ይገባል

ቡሌ ሆራ፤ሰኔ 14/2017 (ኢዜአ)፡-ምሩቃን የቀሰሙትን እውቀት የሕብረተሰቡን ችግሮች በሚፈቱ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊያውሉት እንደሚገባ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ስራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ ገለጹ።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ለ14ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 232 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
ከተመራቂዎች መካከል 13ቱ በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆኑም ተነግሯል።
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ እንደገለጹት ፤ ተቋሙ በግብርና፣ በማዕድን፣ በሀገር በቀል እውቀትና በጤና የትኩረት መስኮችን በመለየት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ቴክኖሎጂ የማፍለቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርትን በሚመለከት የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሄደ።

ሚያዚያ 11/2017 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከል ከሆኑት አንዱ ጤና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዘርፋ በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ በሚሰጡ ትምህርት ፕሮግራሞች ዙሪያ የኮሌጁ መምህራን እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የሥርዓተ ትምህርት ግምገማና ፍተሻ ተካሂዳል።

መንግስት በአሁኑ ሰዓት ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመሆኑ ይህንኑ በመደገፍ እንዴ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በጥራቱ ዙሪያ የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት እና በጤና ኢንስቲትዩቱ በባዮ ሜዲካል ላብራቶሪና በጄነራል ፓብሊክ ሄልዝ የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመጀመር ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ስለመሆኑ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጤና ኢንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ አስረድቷል።

Pages