የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ
*****
በዉይይት መድረኩ ላይ በአገራዊ እና በተቋማዊ የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ በተባባሪ ፕሮፌሰር ጫላ ዋታ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የቀረበዉ የመነሻ ሀሳብ ጭብጦች፡ የ2015 ዓ.ም በአገራዊ የትኩረት አቅጣጫ አንኳር ጉዳዮች፤ የትምህርት ዘርፉን ቀጣይ አቅጣጫዎች ለምሳሌ፡-የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ማረጋገጥ፣ሌብነትንና ብክነትን መታገል፤ ፉትሃዊ ቅጥር፣ ምደባና አገልግሎት ማረጋገጥ፤ አካባቢያዊነትን መታገል፤ ፖለቲካና ትምህርትን መለየት-ሴኩላሪዝምን ማረጋገጥ፤ ራስ-ገዝነትን እና የቦርድ ሚና ማጠናከር ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡
በተቋማዊ ደረጃ ከሚታዩ ክፍተቶች ጋር በተያያዘ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም፤ የሃብት አስተዳደር ተጠያቂነት ደካማ መሆን እና ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ አለመስጠት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡
እንደ ቀጣይ ተቋማዊ ተግባራት ደግሞ የልህቀት ጉዞ አመራር ስትራቴጂ፣ የትምህርትና አገልግሎት ጥራት ማጎልበቻ ዕቅድ ማዘጋጀት፤የ2014 ዓመታዊ ሪፖርት ማዘጋጀትና መገምገም፤የ2015 ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማጸደቅ፤ የራስ ገዝነት የትኩረት መስክ ልየታ ስትራቴጂ መንደፍ፤ የተመራቂ ተማሪዎች ምረቃ መርሃግብር ማሰናዳት እና የመሳሰሉት ለዉይይት መድረኩ ላይ በመነሻ ሃሳብ ጽሁፍ ላይ ከቀረቡት ናቸዉ፡፡
ሌላዉ ከተማሪዎች አገልግሎት ጋር የተያያዙ፤ ከጠቅላላ አገልግሎት እና ከትምህርት አገልግሎት ግብዓት አቅርቦት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችም ተዳሰዋል፡፡
በካዉንስሉ አባላት በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ጋር ተያይዞ በተነሱ የዉይይት መነሻ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
ከካዉንስል አባላቱ የተነሱ ሀሳቦችና አስተያየቶችን ለ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ እንደ ግብአት በመዉሰድ ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን!!!
ሰኔ 14/2014 ዓ.ም
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ