የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
Posted by admin on Wednesday, 17 November 2021የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡሌ ሆራ ቅርንጣፍ ጋር በመተባበር ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያዎች በኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ ጋር በተያያዘ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናዉ ላይ ዶ/ር ታምሩ አኖሌ (የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ) ፣ዶ/ር ሮባ ደንቢ (የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ) እና ዶ/ር ጉሚ ቦሩ (የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት) ተገኝተዋል፡፡
የኤፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባወጣው አዋጅ መሰረት የፌዴራል ፋይናንስ ተቋማት ማንኛውንም ክፍያ በዲጅታል ኤሌክትሮኒክሲ የክፍያዎች መረብ መፈፀም እንዳለበት ይደነግጋል::