በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ "አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ "

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ "አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ!" በሚል መሪ ቃል በሰሜን እዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመ የግፍ ተግባር ታስቦ ዋለ።
የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ዳርድንበር ከማስከበር ባሻገር ለአለም አቀፍ፣ ለአህጉራዊና ቀጠናዊ ሠላም መረጋጋትም የደም እና የህይወት ዋጋ በመክፈል ለሠላም ዘብ የቆመ የሀገር ደጀን ነዉ።
የሀገርን ድንበር እና ሉዓላዊነት ለማስከበር ከ20 ዓመታት በላይ የሀገርን ዳር ድንበር ሌት ተቀን ሲያስከብር በቆየው የሰሜኑ ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ዘግናኝ እና ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ጥቃት ተፈጽሟል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ይህንን ቀን በማሰብና የሕይወት መስዋዕትነት ለከፈለውና እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነቱን ለማረጋገጥ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም ከማለዳው 2:30 ጀምሮ በዩኒቨርስቲው ኦዳ አዳራሽ ፊት ለፊት መርሃግብሩን አካሂዷል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠናቸውን 511 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠናቸውን 511 ተማሪዎችን አስመርቋል። 

ከተመራቂዎቹ 363ቱ ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ከሕግ ት/ቤት በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ቀሪዎቹ 148 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ በመደበኛ ፕሮግራም ስልጠናቸውን እንደተከታተሉ የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዳንኤል ሰይፉ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። 

ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 74ቱ (22 በ2ኛ ዲግሪ) ሴት ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። 

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ 844 ተማሪዎችን ባለፈው ሰኔ በመጀመሪያ እና 2ኛ ዲግሪ ማስመረቁ ይታወሳል። 

Pages