ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የካዉንስል አባላት ፣ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በእቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት እንዲሁም አተገባበር ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ስልጠናው የተሰጠው በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ጫላ ዋታ ሲሆኑ፤ የእቅድ ዝግጅት ሂደት፣ የእቅድ መነሻ፣ የእቅድ አላማና ሰነድ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዉበታል።
ተቋሙ ከመደበኛ እቅድ በተጨማሪም በልዩ እቅድ ታግዞ በርካታ ለዉጦችን ማምጣት እንደቻለ የገለጹት ፕሬዘዳንቱ በእቅድ ታግዞ መስራት ተቋማዊ እና ሀገራዊ ለውጥ ከማምጣቱ በተጨማሪ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል ብለዋል።
ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጫላ ዋታ ከሀገሪቱ የ10 አመት መሪ እቅድና ፍኖተ ብልጽግና ጋር አያይዘው የተቋሙን ተደራሽ ግቦችና ስትራቴጂካዊ ተግባራትን በሰፊው አብራርተዋል ።
በዕቅድ ታግዞና የበጀት መርህን ጠብቆ በትጋት መስራት የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ ፣ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የተቋሙን እሴቶች እውን ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ፕሬዚዳንቱ በአጽንኦት አንስተዋል።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለዩኒቨረሲቲው በተለያየ ክፍል ባለሙያዎች እና የሰዉ ሀብት ልማት አስተዳደር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

የስልጠናው ትኩረት ከኦዲት ግኝት የፀዳ ተቋም ለመፍጥር በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሆን፤ በገንዘብ ሚኒስቴር የኦዲት ኢንስፔክሽን ባለሙያ በአቶ መኮንን መኩሪያ ስልጠናው ተሰቷል።
የበጀት ክትትል፣ የተከፋይ ሂሳብ፣ የግዥ፣ የንብረት አያያዝና አጠባበቅ ስርዓት እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ የፋይናንስ አጠቃቀም እና አተገባበር የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች በስልጠናው ዉስጥ ተካተዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴርን ደንብ እና መመሪያ ህጉን በጠበቀ መልኩ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማክበርና ለማስከበር በሚያስችሉ ፅንሰ ሀሳቦች ላይም ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ አስተዳደር ሠራተኞች እና ባለሙያዎች በፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

በስልጠናው ላይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቦሩ ህርባዬን ጨምሮ በረካታ ቁጥር ያላቸው የፋይናንስ ባለሙያዎች ተሳተፈዋል::
በስልጠናው በፋይናንስ አስተዳደር፣ በበጀት ምንነት፣ በክፍያ ሁኔታዎች፣ በጥሬ ገንዘብ አጠቃቀም፣ የበጀት መርህ እቅድን ከበጀት ጋር ማስተሳሰር በሚሉ እና በሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናው ተሰጠቷል::
በስልጠናው የፋይናንስ አስተዳደርን ለማዳበር እና ውጤታማ የበጀት አጠቃቀምን ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቄሜታ እንዳለው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተሩ በስልጠናው ላይ ገልፀዋል::
በተቋሙ ዉስጥ ለሚከናወኑ የለውጥ ስራዎችና አጠቃላይ የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የበጀት አጠቃቀምና ምንነትን ማወቅ አስፈላጊ ስለመሆኑም አንስተዋል::

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡሌ ሆራ ቅርንጣፍ ጋር በመተባበር ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያዎች በኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ ጋር በተያያዘ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናዉ ላይ ዶ/ር ታምሩ አኖሌ (የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ) ፣ዶ/ር ሮባ ደንቢ (የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ) እና ዶ/ር ጉሚ ቦሩ (የምርምርና የማህበረሰብ  አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት) ተገኝተዋል፡፡
የኤፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባወጣው አዋጅ መሰረት የፌዴራል ፋይናንስ ተቋማት ማንኛውንም ክፍያ በዲጅታል ኤሌክትሮኒክሲ የክፍያዎች መረብ መፈፀም እንዳለበት ይደነግጋል:: 

Pages